የአክሲዮን ማህበሩ ራእይ
በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭና አካታች የፋይናንስ ተቋም ሆኖ ማየት ነው፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ ተልእኮ
የአድዋ ድል ማይክሮፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያንን የፋይናንስ ደህንነት ለማሻሻል እንደ ቁጠባ፣ ብድር፣ ጥቃቅን ብድሮችን የአገር ዉስጥ ገንዘብ ማስተላለፍና የክፍያ አገልግሎቶች እንዲሁም የንግድ ስራ እውቀትን በማስተዋወቅ የህብረተሰቡን ፋይናንስ ዋስትና ማሻሻል ነው፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ እሴቶች
- ሀገራዊ እሴቶች ላይ በማተኮር ደንበኞችን ማስቀደም፣
- በሰብአዊነትና በርህራሄ ማገልገል፣
- ለሰራዊት አባላት በጡረታና በክብር ለተሰናበቱ የጦር አባላት ቅድሚያ በመስጠት የፋይናንስ ደህንነታቸውን ለማሻሻል ቁርጠኝነትን ማረጋገጥ፣
- ብዛህነትንና ማካተትን መቀበል እና ማክበር፣
- አገልግሎት በመስጠት ሂደት ግልጽነትና ተጠያቂነትን በማስፈን ታማኝነትን ማረጋገጥ፣
- የደንበኞች ፍላጎት በማሟላት ላይ ቅድሚያ መስጠት፣

